እግዚአብሔር ክበር ክበር

-

እግዚአብሔር ክበር ክበር
አምላኬ ክበር ክበር
ለአንተ ይገዙ ሰማይ ምድር /2/

1. አእዋፍ አራዊት ይዘምራሉ
ታላቅነትህን ያወራሉ
መላዕክት በሰማይ ያከብሩሀል
ፍጥረታት በምድር ይገዙልሀል

2. እኛም ቆመን እንዘምራለን
ታላቅነትህን እናወራለን
እንሰግዳለን ፊትህ ተንበርክከን
እግዚአብሔር ሆይ እናከብርሃለን

3. ሰማይ እና ምድር ሁሉ ያልፋሉ
ሳይቀሩ ፍጥረታትም በሙሉ
ቃልህ ለዘላለም ፀንቶ ይኖራል
ታላቅ ነህና ክብር ይገባሃል

4. እንዘምር ስለ ታላቅነትህ
እናውራ ስለ ኃያልነትህ
ከእግሮችህ ስር ወድቀን እናክብርህ
ዛሬም ለዘላለም እንገዛልህ

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top