ኧረ ለምን ዝም እላለሁ
ኧረ ለምን ዝም እላለሁ
ጌታ አስቦኛል አወራሁ
ሳላቋርጥ እጣራለሁ
ወደ አምላኬ እጮሀለሁ
ጌታ አስቦኛል አወራለሁ .
በመንገድ ቁጭ ብዬ እየለመንኩኝ
የኢየሱስ ዝና ከሰዎች ሰማሁኝ
ለምን እዘገያሁ ፈጥኜ ልጣራ
ፈዋሽ የሆነ አምላኬ ከጎኔ አልፏልና
ኢየሱስም ድምጼን ሰምቶ እጅግ ፈለገኝ
ሰዎች ያገዱኝን ምስኪኑን ሲጠራኝ
ምን ትፈልጋለህ ብሎ ሲጠይቀኝ
ማየት ነውና ፈጥነህ እራራልኝ
በትንሿ እምነቴ አርሱም ተደስቶ
የምሻውን ሰጠኝ እጅጉም አብዝቶ
ቀን ወጣልኝና ይኸው ዛሬ አየሁኝ
ተአምር ተሰርቷል ጌታን አክብሩልኝ
የእግዚአብሔር በረከት ልጆችም የሉኝ
ፈኒና በነገር ስታማርረኝ
ከአመት ወደ አመት መፅናናት እርቆኝ
ወደ አምላኬ ጮኽኩኝ እያለቀስኩኝ
የሰራዊት ጌታ እኔን ሲያስበኝ
መከራዬን አይቶ ከቶ አልረሳኝ
