1. ማንም የተጠማ ቢኖር ወዳንተ ይመጣል
የህይወት ወንዝ ውሃ በሕይወቱ ይፈልቃል /2/
አንተ የሕይወት ብርሃን ነህ
በአንተ የሚያምን በጨለማ አይኖርም
መልካም እረኛ ኢየሱስ አንተ ነህ
ስለኔ ስትል ነፍስህን የሰጠህ
ጌታ ሆይ ካንተ ወዴት /2/ እሄዳለሁ
ኢየሱስ ሆይ ካንተ ወዴት /2/ እንሄዳለን
አንተ የህይወት ምንጭ ነህና
ከአንተ የሚጠጣ አይጠማምና
ሃሌ ሉያ
2. ስላም ዕረፍት የናፈቀው ወዳንተ ይመጣል
ሰላምና ዕረፍትን ከአንተ ያገኛል /2/
በአንተ የሚያምን ከቶ አይታወክም
ሰላም ከእርሱ ዘንድ ማንም አይወስዳትም
የሰላም ንጉስ ኢየሱስ አንተ ነህ
ለኔ የሰላም ህይወት የሰጠኸኝ
3. በባርነት ቀንበር ያለው ወዳንተ ይመጣል
ከቀንበሩ ተፈትቶ ነፃነት ያገኛል /2/
ጌታ ሆይ አንተ የፍቅር አምላክ ነህ
ህይወት የሚሰጥ ብርሃን የሞላብህ
የነፍሴ ፈዋሽ ኢየሱስ አንተ ነህ
በመስቀል ሞተህ ነፃ ያወጣኸኝ
