ክብሩን ትቶ ከላይ ወደኔ መምጣቱ
እራሱን አዋርዶ በረት መወለዱ
ፍቅር /3/ እኮ ነው ምክንያቱ
ከላይ መጣ ሞተ ለእኔ
ተቀበለ እርግማኔን
የት ይገኛል እንደርሱ ፍቅር
እራሱን ሰጥቶ ሌላ የሚያድን /2/
ሃይል እያለው የዋሹበት
እያፌዙበት ሲያሰቃዩት
አንዲት ቃላት ሳይናገር
አሸነፈ ሁሉን በፍቅር /2/
በተግባሩ ስኬታማ
በጥበቡ አይታማ
ፍቅር ኣውርዶ ጥልን ኣራቀ
ነገስታትን ኣስታረቀ /2/
ክቡር ሳለ ተዋረደ
ያለበደሉ ወደ ፍርድ ሄደ
ለመስቀል ሞት ያደረሰው
ሌላ ሳይሆን ፍቅር እኮ ነው/2/
