ወንጌሉን ንገሩ በጨለማ ለሚኖሩ
ኢየሱስ ያድናል ያበራል ብርሃን በሉ
ወንጌሉን አብስሩ በጨለማ ለሚኖሩ
ኢየሱስ ያድናል ያበራል ብርሃን በሉ
የወንጌሉ አደራ ታላቅ ነው እወቁ
ቢመችም ባይመች የሱስን ስበኩ
ያላመኑ ይስሙ ይዮ ይሄን ብርሃን
ሲኦል ባዶ ትቅር ሁሉም በእርሱ ይዳን
አላያችሁም ወይ እውራን ሲበሩ
የእግዚአብሔር አብ እጆች ታሪክን ሲሰሩ
ነፍሱ ለደረቀ ዛሬም የሚያረካ ውሃ
ከወንጌሉ ይፈልቃል ስበኩ ይህን ቃል
አክሊላችን የሱስ ዛሬም ያከበርነው
በእግዚአብሔር አብ ቆሞ ምስክራችን ነው
በማዕዱ ግብዣ ያገለግለናል
እስከዘለዓለም ያም እረፍት ይሆናል
