ውዴ ሆይ ውዴ ሆይ /3/
አንተ ውብ ነህ /2/
ውዴ ሆይ ቀኑ እስኪነፍስ
ውዴ ሆይ አንተ ውብ ነህ
ውዴ ጥላውም እስኪሸሽ
ውዴ ሆይ ድረስ ተመለስ
ውዴ ሆይ እኔ ተኝቻለሁ
ውዴ ሆይ ልቤ ግን ነቅቶአል
የውዴ ቃል ደጁን ይመታል
ውዴ ሆይ አባክህ ላግኝህ
ውዴ ሆይ ከፍቅርህ የተነሳ
መታመሜንም እንድነግርህ
ውዴ ሆይ እጅጉን ጣፋጭ ነህ
ውዴ ሆይ ልቤን ማርከኸዋል
ያንተ ሆኖ እንዲኖር አርገሃል
