የሕይወት መሻት ስጠኝ

36

የሕይወት መሻት ስጠኝ
በመንፈስህ ጌታ ምራኝ
አስተካክለህ አቁመኝና
ላስከብርህ ባንተ ልፅና

በአካሄዴ ባረማመዴ
ልኑር ጌታ አንተን አክብሬ
ይህ ነውና ፍላጎቴ
ፈጽምልኝ ውድ አባቴ

ብዙ ኃጢአት ሰርቻለሁ
አንተን ጌታ በድያለሁ
ስለዚህ ምህረትህን እሻለሁ
ወደ አንተ መጥቻለሁ

ካንተ ሌላ መዳን የለም
ያላንተ መኖር አይቻልም
አንተን ብቻ መርጫለሁ

ካንተ ጋራ እኖራለሁ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top