የመላኩን ቃል ኣምነሽ የተቀበልሽ
የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ
እንዳልከው ይሁን ያልሽ
የአምላክን ፍቃድ በትጋት የፈፀምሽ
አ የአምላክ እናት እመቤታችን ነሽ
ኦ ማርያም የአምላክ እናት
ኦ ማርያም ንዕእት እመቤት
ኦ ማርያም ትውልድ የሚያከብርሽ
ኦ ማርያም ኣማልጅን ከልጅሽ
በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘሽ
የኢየሱስ ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ
የመንፈስ ቅዱስ ሐይል ጋርዶ የፀለለሽ
በአምላክ የተመረጥሽ ድንግል አንቺ እኮነሽ
በነፍስና ስጋሽ እግዜርን ያከበርሽ
በመንፈስሽ አምላክ በእርሱ የተደሰትሽ
የእርሱን ታላቅነት ክብር የመሰከርሽ
የአምላክ አገልጋይ እመቤታችን ነሽ
