1. የድሮ እኔነቴን ረስቼ ሰው ሆኜ
ዛሬ በከፍታው ላይ ቆሜ
እፎይ ብዬ እኖራለሁ
አልሰጋም የሚያዘውን ይዣለሁ
ይዣለሁ /2/ ለምን እሰጋለሁ /2/
የትላንቱ ጌታ ዛሬም ጌታዬ ነው
ይዣለሁ /2/ ለምን እሰጋለሁ /2/
የትላንቱ የሱስ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው
ትላንት እንደረዳኝ ዛሬም አለልኝ
ትላንት እንዳነሳኝ ዛሬም አለልኝ
ትላንት ሰው ያረገኝ ዛሬም አለልኝ
ትላንት ያከበረኝ ዛሬም አለልኝ
እኔ ——-እኔ አልፈራም
እኔ አልፈራም አልሰጋም /2/
2. አንዴ ቀርቦኛል ኢየሱሴ ላይርቀኝ
ንብረቱ ገንዘቡ አድርጎኝ
የተከፈተም በር አሳየኝ
ባረገው በትንሿ ደግሞ እንዳይገርመኝ
እንዳይገርመኝ /2/ እጄን በእጁ ያዘኝ
አለሁልህ እያለ ልቤን ኩራት ሞላኝ
እንዳይገርመኝ /2/ ልቤን ድፍረት ሞላኝ
እንደትላንትናው ዛሬም ሊረዳኝ ነው
3. ጊዜያዊ ተሰባሪ አይደለም ምርኩዜ
ሁኔታዎች ባስገደዱኝ ጊዜ
ከልጅነት ያጠመደኝ
አሁንም ሳይቆረቁረኝ በእጁ ላይ ነኝ
በእጁ ነኝ /2/ አንድም ሳይጎልብኝ
እንዳመሌ ይዞ ይኸው ለዚህ አበቃኝ
በእጁ ነኝ /2/ ዛሬም በእጁ ላይ ነኝ
ላልለቀው ላይለቀኝ በፍፁም ላይረሳኝ
