የፍቅር ቅኔ

97

ድንቅ አድራጊ ነህ ሚመስልህ የለም
በምድር በሰማይ ለዘለዓለም
ፈውሰኸኛል እኔን ከክፉ ደዌዬ
ላወድስህ ጌታ በፍቅር ቅኔዬ

የፍቅር ቅኔ ልቀኝልህ
መልካም ቃላትን ላፍልቅልህ
በጣፋጩ ዝማሬ ላወድስህ
አውቃለሁኝ ጌታ ይህም ሲያንስብህ /3/

ሥራህ አስደናቂ አስገራሚ ጌታ
በክንድህ ድጋፍ ብርቱ መከታ
አድርገህልኛል ብዙ በሕይወቴ
እቀኝልሃለሁ ምስጋናን ከልቤ

ቅን ፈራጅ አምላክ በሁሉም ቦታ
ማንስ ይችላል አንተን ሊረታ
ቀንበሬን ሰባብረህ ነፃ አውጥተኸኛል

አቀኝልሃለሁ ሰላም ሰጥተኸኛል

ለየት ያለ ነው ፍቅርህ ቅባትህ
ሞገስ የሞላው መቅደስ ዙፋንህ
ቢተረክ የማያልቅ ብዙ ሰጥተኸኛል
እቀኝልሃለሁ ክብር ይገባሃል

ሃብቴ ነህ አምላክ ቅርሴ ነህ ጌታ
ሁሉት ቻይ የሆንክ የሌለህ አቻ
ምን ልከፍልህ ይሆን ለዚህ ሁሉ ውለታ
ሌላ ምን እላለሁ ልቀኝልህ ጌታ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top