ገሩ ልብህ ምህረት የሞላው
በሐጥያት እኛ ስንወጋው
እምቢም ኣይል ማረኝ ለሚለው
ጥቂት እንኳን ትንሽ ቂም የለው
ኦ የሱስ
በቄስ ጆሮ ያቀረብነውን
የኛን ስራ ምናምቴውን
በይቅርታህ አጥፋው አሁኑን
ካለማወቅ እንድትቆጥርልን
ኦ የሱስ
በኛ በኩል ምንስ የት አለና
በአንተ በኩል ምረት ሞልቷልና
በይቅርታህ ኣሁን በል ቶሎ ና
ካንተ ጋራ ፍቅር እንዲፀና
ኦ የሱስ
ንገስ ንገስ የአንተ መንግስት ይስፋ
ሰው ልጅ ዘር አንድ እንኳን
እንዳይጠፋ
በአለም ሁሉ አንተ ሁነን ተስፋ
ክፋት ቀርቶ የአንተ መንግስት ይስፋ
ኦ የሱስ
በክፉ አመል ስንቸነክርህ
ከአይሁድ ጋራ ተባብረንብህ
ዳሩ ግን አንተ ምንግዜም ቸር ነህ
ይቅር በለን በገፋ ልብህ
ኦ የሱስ
