ገና ይመለካል

103

ለሚጠይቁት መልስ ለማይሰጥ
ጌታ ነኝ ብሎ ራሱን ለማይሰጥ
እኔስ አልሰግድም ለተቀረፀው /2/
እያለ ጌታ በኔ የሰረፀው

እኔ የማመልከው ጌታን ጌታን ብቻ
የማከብረው ጌታን ጌታን ብቻ
የማነግሰው ጌታን ጌታን ብቻ
እርሱን እርሱን ብቻ

ድቅድቅ ጨለማ አያስፈራኝም
ከእንግዲህ ብርሃን ሆ ለኔ አያሻኝም /2/
በግንባሬ ላይ የተቀባው ደም
መለያዬ ነው ስርዓት አይደለም

ገና ይመለካል ገና /6/
እስኪ ይግረመው ይስማ ጠላቴ
ቆሜ ስዘምር ሆ እኔስ ላባቴ
ገና ይጨምራል ብዙ ምስጋና /2/
ጌታዬ ብቻ ሆ ሁሌም ገናና
ገና ይመለካል ገና /3/
ገና ይከበራል ገና /3/
ገና ይወደሳል ገና /3/
ገና ይዘመራል ገና /3/
ገና ገና ይመለካል ገና /2/

ገና ገና ይከበራል ገና /2/
ገና ገና ይወደሳል ገና /2/
ገና ገና ይዘመራል ገና /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top