ጉልበቴ በረታ

237

ሳስብ ወደኃላ ትላንተ ያለፍኳቸው
የሕይወት ተራራ ብዙ ብዙ ናቸው
እንዳለፈ ውሀ ስንቱ ረስቼ
ሁሉም ሠላም ሆነ በርሱ በወዳጄ
ጉልበቴ በረታ /2/
አንተን ታምኖ ጌታ

የቱን ብዬ የቱን እተዋለው
የርሱ ውለታ ከአዕምሮ በላይ ነው
አልጨርሰው እኔስ ተናግሬ
መልካም ስራው ስወለድ ጀምሬ

ሆነኽልኝ እናትና አባቴ
እያሞላህ ሁሉን ፍላጐቴ
ደህንነቴ ሆንክልኝ ዋስትና
የትላንቱን ሁሉን ረሣሁና
ባንተ ነው ለዚህ መድረሴ
ባንተ ነው ሆነህ ሞገሴ
ባንተ ነው ታክብርህ ነፍሴ

ከጨለማ ከሆታ ያወጣኽኝ
በብርሃንህ ብርሃን ያሳየህኝ

ዛሬም ይኽው እመሰክራለሁ
ያዳንከኝን አመሰግናለው

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top