ገና ከጀምሬ ከመነሻዬ
እግዚአብሔር ነው መታመኛዬ/4/
ጌታን ይዤ በእርሱ ብርታት
አገኘሁኝ የህይወት ፅናት
መጀመርያ መጨረሻዬ
የህይወቴ ነው መመሪያዬ
ጌታን ይዤአለሁ እርሱን ይዤአለሁ
አይፈራም ልቤ ድል አደርጋለሁ/2/
እግዚአብሔር ተናግሯል ለምን ልጠራጠር /2/
እንዲህ ይሆናል ብዬ ልቤም አይሽበር /2/
ሥጋት አይገባኝም ላፍታ
እያለ የሰራዊት ጌታ /2/
የተሸነፈ የለም ጌታን ይዞ አሃሃ እርሱን ይዞ
የወደቀ የለም ጌታን ታምኖ አሃሃ እርሱን ታምኖ
ድል ነው እንጂ አይኖርምሽንፈት
እግዚአብሔር በሚገኝበት /2/
ጌታን ይዤአለሁ
ቀይ ባህር ከፌቴ ቆሞ እንደ ተራራ /2/
አላሳልፍ ብሎ ልቤን ቢያስፈራራ /2/
አለ ሁሉን የሚችለው
ታዲያ ፍርሀቱ ምንድን ነው
ወጥቶአል እግዚአብሔር ከፊቴ
ጠፍቶአል የለም እንቅፋቴ /2/
እግዚአብሔር የፈቀደውን ልቤም የተመኘውን
ከንአንን እወርሳታለሁ /2/
አይቀርም ህልም ሆኖ ከንአንን እወርሳታለሁ /2/
ጌታን ይዣለሁ እርሱ ይዣለሁ
አይፈራም ልቤ ድል አደርጋለሁ
