የጎልጎታ ስቃይ ተካፋይ አንድሆን
ፍቅርህን አልረሳም ለኔ የዋልከውን
የማልረሳው ፍቅር የሱስ የከፈልከው
በጅራፍ መገረፍ በጦር መወጋት ነው
ስለ በደሌና ስለሀጢያቴ ሞቶ
እንድገባ ጠራኝ የሰማይ በር ከፍቶ
የቀራኒዮ አርማ በልቤ ያተመው
ማንም የማይሽረው ዘለዓለማዊ ነው
መስቀል መሸከሙ ትርጉም ያልገባቸው
ይስቁበት ነበር ተራ ሰው መስሏቸው
ግን አልተረዱትም ያንን ታላቅ ሚስጢር
የተጓዙበትን ከሞት ወደ ክብር
ብዙዎች ንቀውት ወደ ጎን ቢተውት
እንደ ተራ ወሬ ኣይጠቅመንም ቢሉት
ለኔ ግን ክብር ነው ያሞትና ጭንቀት
ከአምላኬ የወረስኩት የመስቀል ነፃነት
