ፍቅር የማውቀው ይሄ ነው
ራሱን አይወድም ጨዋ ነው
የሚያዝን ልቡ ሚራራ
ችግር ላጠቃው መከራ
ፍቅርን ያወቀ እስኪ ማነው
ራሱን ስለፍቅር ያኖረው
ለስጋው ክብር የማይኖር
የተባረከ በእግዚአብሔር
አቤት ስንት አላ በምድር ላይ
የበደል መዓት ገኖ ሚታይ
ሰው በሰው ላይ እየጨከነ
በችግር ስቃይ እየኮነነ
እግዚአብሔር ይሄን ይመለከታል
በፈጠረው ሰው እጅጉን ያዝናል /2/
በረሃብ ችግር ወገን ሲጎዳ
ማነው የሚያዝን ማነው ሚረዳ
ጩኸቱን ሰምቶ የሚደርስለት
ለዚህ የበቃ ፀጋው በዝቶለት
እሱ ነው ፃድቅ የተባረከ
ልቡ የተነካ ጌታ የረዳው /2/
ባለው እውቀት ላይ ዕውቀት ቢጨምር
ሀብቱ ቢበዛ ቢሰራ ክምር
ፍቅር ከሌለው ባያይ ወንድሙን
ታዲያ ምንድነው የቱ ነው ጥቅሙ
እግዚአብሔር ይሄን ይመለከታል
የሰውን ክፋት በርግጥ ይጠላል /2/
