ነፍሴ በእግዚአብሔር
ነፍሴ በእግዚአብሔር ሀሴት ታደርጋለች
መንፈሴም በአምላኬ ሁሌ ትደሰታለች
እኔን ዝቅተኛ ባሪያውን ተመልክቷል
ትውልድ ሁሉ ቅድስት ብፅዕት ይለኛል /2/
- ዝቅ ያለውን ሊያነሳ ትዕቢተኛን ለጥል
ጌታ ኢየሱስ መጥቷል ምስኪንን ሊያከብር
እግዚአብሔር ሞገሴ ክብሬ ሆኖልኛል
የከበረው ንጉሥ በእኔ ሊያድር ወዷል
ነፍሴ በእግዚአብሔር ሀሴት ታደርጋለች
መንፈሴም በአምላኬ ሁሌ ትደሰታለች
እኔን ዝቅተኛ ባሪያውን ተመልክቷል
ትውልድ ሁሉ ቅድስት ብፅዕት ይለኛል /2/
2. ከብዙዎች መሐል ታማኝ አድርጎ ቆጥሮኝ
የማዳኑን ምስጢር ተካፋይ አረገኝ
ነፍሴም ተማረከች በሆነላት ነገር
ጌታ የዋለላትን ትመስክር ዘወትር
ነፍሴ በእግዚአብሔር ሀሴት ታደርጋለች
መንፈሴም በአምላኬ ሁሌ ትደሰታለች
እኔን ዝቅተኛ ባሪያውን ተመልክቷል
ትውልድ ሁሉ ቅድስት ብፅዕት ይለኛል /2/
3. ብርቱ የሆነው ጌታ ድንቅ አድርጎልኛል
የቅዱስ መንፈሱ እግዚአብሔር ዳሶኛል
የመለኮት ኃይሉን ጥበቡን አሳየኝ
ማዳኑን ለማየት በኩር አደረገኝ
አትፍሪ ማርያም
አትፍሪ ማርያም ፀጋን ተሰጥቶሻል
ልኡል እግዚአብሔር ይፀልልሻል
ወልድ አምላክ ይመጣል
ከአንቺ ይወለዳል
አዳኝም ይባላል
ማርያም እርሱን እርሱን በይ
ስሙት ስሙት ሕይወት ነው ለማያውቁት
ማርያም እርሱን እርሱን በይ
ስሙት ስሙት መንገድ ነው ለማያውቁት
ንገሪ ለማያምኑት አብሳሪ ለማያውቁት
ጌታ ነው መስክሪለት ንጉስ ነው ለታመኑት
- ስበኪ በአደባባይ እውነቱን ንገሪ ይታይ
እግዚአብሔር በኢየሱስ ያለውን አላማ
አትፍሪ ንገሪ እስኪ ሁሉም ይስማ
እግዚአብሔር ለፍጥረት ያለውን አላማ
አትፍሪ ስበኪ አስኪ ሰይጣን ይስማ
ማርያም እርሱን እርሱን በይ
ስሙት ስሙት ሕይወት ነው ለማያውቁት
ማርያም እርሱን እርሱን በይ
ስሙት ስሙት መንገድ ነው ለማያውቁት
ንገሪ ለማያምኑት አብሳሪ ለማያውቁት
ጌታ ነው መስክሪለት ንጉስ ነው ለታመኑት
2. ግሩም ነው ሞትን ድል ነስቶ
አልቀረም ኢየሱስ ተረስቶ
በጸሎትሽ ፍሬ መንፈሱን ሰቶሻል
ማርያም ንገሪ እውነቱን ይዘሻል
በጸሎትሽ ትጋት መንፈሱን ሰቶሻል
ስለሱ መስክሪ አዳኝ ልጅ ወልደሻል
አትፍሪ ማርያም ፀጋን ተሰጥቶሻል
ልኡል እግዚአብሔር ይፀልልሻል
ወልድ አምላክ ይመጣል
ከአንቺ ይወለዳል
አዳኝም ይባላል
ማርያም እርሱን እርሱን በይ
ስሙት ስሙት ሕይወት ነው ለማያውቁት
ማርያም እርሱን እርሱን በይ
ስሙት ስሙት መንገድ ነው ለማያውቁት
ንገሪ ለማያምኑት አብሳሪ ለማያውቁት
ጌታ ነው መስክሪለት ንጉስ ነው ለታመኑት
ስላንተማ
አዝ. ስላንተማ ብዙ ምናገረው አለኝ /2/
የትኛውን አንስቼ የትኛውን እተዋለሁ
ጌታዬ ሥራህ እኮ ከአእምሮዬ በላይ ነው
1. እግ/ር ሃያል ነህ ማንም አትንቅም
ደካማን በመጣል አንተ አትታወቅም
ከጥንት የሰማነው በአይናችን ያየነው
ጻድቅነትህን እና ሰውን መውደድህን ነው /2/
2. ጥንት አባቶቻችን ሥራህን አወሩ
ድንቅ ታምራትህን እየመሰከሩ
ሥራህ እግ/ር ሆይ ከአእምሮ በላይ ነው
እኔ ምስክር ነኝ በአይኔ አይቻለሁ /2/
3. የማወራው አለኝ የምመሰክረው
ስላንተ ምህረት ፍቅር የምናገረው
ስለሰው ልጅ ሃጢያት ልጅህን ሰጥተሃል
በእውነተኛ ፍቅርህ እኛን አድነሃል /2/
ከአእምሮ በላይ ነው ፍቅርህ
እኛን መውደድህ /2/
ክበር እንጂ ሌላማ ምን እንላለን
በላይ በላይ ምስጋናን እንጨምራለን
በላይ በላይ ክብርን እንጨምራለን
ንገስ እንጂ ሌላማ ምን እንላለን
በላይ በላይ ምስጋናን እንጨምራለን /2/
ልነሳና ልነሳና ላክብርህ
ምክንያት አለኝ ብዙ ብዙ
ምክንያት አለኝ ክበር /3/
ምስጋና አሃሃ ላንተ ነው ክብርም አሃሃ ላንተ ነው
አምልኮ ኦሆ ሆ ላንተ ነው ስግደትም ላንት ነው
ያረክልን ብዙ ነው ጌታ አሃ ሃ /4/
ውዳሴ ላንተ ነው ቅዳሴ ላንተ ነው
ጭብጨባ ላንተ ነው እልልታ ላንተ ነው
ያረክልን ብዙ ነው ጌታ አሃ ሃ /4/
