አንድ ይሁን አላማችን

164

የኛ ክርስቲያኖች ጉዞአችን ብሩህ ነው
የወንጌሉን ትምህርት መሪያችን እርሱ ነው
የታላቅ መምህር ተከታይ ነንና
እንጓዝ ክርስቲያኖች በብርሐን ጐዳና

ክርስቲያኖች አንድ ይሁን አላማችን
በእምነታችን ፀንተን መቆማችን

ዳገት ቁልቁለት አቀበቱን ጨርሰን
ሕይወት ላለው ቃሉ ምቾትን ሰውተን
አላማችን ሰምሮ ተቃንቶ እንድናየው
በአንድነት እንሂድ ህብረት ሐይላችን ነው

በአለም ብልጭልጭ ከቶ ሳንደላደል
የሚያልፈውን ሕይወት የማያልፈውን ማዋል
ይኸው ነው ትርጉሙ አርማችን ክርስቲያኖች
የፍቅር የእምነት የተስፋ ተጓዦች

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top