በእምነት ተናገራ እመን እንጂ አትፍራ
ቃሉን ታመንና ሂድ በድል ጐዳና
ላመኑት አያሳፍርም ሰምቶ ቸል ቸል አይልም
ይራራል ለጠበቀው ፍቅር ነው አያስችለው
የውጤቱ ቀመር አይደረስበት
በእውነት በመንፈስ ይገኛል በእምነት
ልቦናህ ይከፈት ላከው ወደ ጌታ
ለጭንቅህ ማስረሻ እርሱ ነው እፎይታ
በፍፁም ልቦና በእርሱ ብትታመን
አለ የድል ጌታ እረፍ ተደላደል
ዙሪያህ ያለው ነገር ተሰፋ ቢያስቆርጥህ
ወደላይ ተመልከት አባተ እኮ አለህ
አምላኩ የሆነለት መመኪያ ኩራቱ
እግሩ አይናወጥም ነው ሁሌ እርሱ ብርቱ
ሁሌም በምስጋና ድል ድል ይላል እንጂ
ፈፅሞ አይናወጥም ሌላ ሌላ ደጅ
