አልሆንም የሌላ

165

አንተ ከወደድከው ከመረጥከው ጋራ
እሆናለው እንጂ አልፈልግም ሌላ
እኔ አልሆንም የሌላ
እኔ አልፈልግም ሌላ

አያታልለኝም የፈርኦን ጮማ
መቼ ሊሆንልኝ አምላኬ እንዳተማ
ሊፈቀው አይችልም የኔ ማንነቴ
የዘር ሐረግ ክንዴ ስሬ መሰረቴ

ከአለም ክብር ዝና ከስጋ ምቾት
መጣልን መርጣለሁ እኔስ በአንተ ፊት
ጊዜያዊ አይደለም ታይቶ የሚጠፋ
አለው ትልቅ ዋጋ የዘለአለም ተስፋ

የከንቱ አይደለም የምድር ዘመኔ
እግዚአብሔር ልትሰራ አላማ አለህ በእኔ
እኔም መርጫለሁ መሆን ከአንተ ጋራ
ሃሳብህን ላገልግል አንተም በእኔ ስራ

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top