በመክሊቴ ብዙ አትርፌ
ታማኝ ሆኜ ላገልግልህ ጌታዬ /4/
በዘመኔ ለአንተ ኖሬ አንተን ብዬ
ላስከብርህ ጌታዬ /4/
ልሁን አገልጋይ ስለአንተ ታማኝ
ሃይልህ ያግዘኝ ኢየሱሴ እርዳኝ
ቀባኝ አብዝተህ ሃይሌ እንዲታደስ
ለአንተ ዝማሬ ቅኔን እንዳፈስ
በዋልኩበት መስክ ስምህን ላስጠራ
ቋንቋዬ ይሁን ስለአንተ ላውራ
ሁንልኝ አንተ ለእኔ አላማዬ
እንዲህ ከሆነ ያምራል ኑሮዬ
ሆኜ እንደልብህ እንዳንተ ሃሳብ
ደስ ኣስኝቼ ጌታ የአንተን ልብ
እንዲህ ማለፍ ነው የእኔ ምኞቴ
ፀጋህን ኣብዛልኝ ይፅና ምኞቴ
