አሳ አጥማጅ ነበርኩኝ

167

ካንተ ተለይቼ ወዴት እሄዳለሁ
አንተ የሕይወት ቃል እንዳለህ አውቃለሁ /2/

1. አሳአጥማጅ ነበርኩኝ ለእለት ጉርስ የምኖር
ና ብለህ ስትጠራኝ የህይወት ቃል ልትሰጠኝ
ወደ ህይወቴ ገብተህ ኑሮዬን ለወጥከው
ሰዎችን እዳጠምድ አገልጋይ አረከኝ

ካንተ ተለይቼ ወዴት እሄዳለሁ
አንተ የሕይወት ቃል እንዳለህ አውቃለሁ /2/

2. መቅበዝበዜን አይተህ መውደቅ መነሳቴን
በአንተ አሳረፍከኝ አድሰህ ህይወቴን
እንዲህ ያለ እረፍት ማን ሊሰጥ ይችላል
እየሱስ ለኔ ግን አትረፍርፈኸዋል

ካንተ ተለይቼ ወዴት እሄዳለሁ
አንተ የሕይወት ቃል እንዳለህ አውቃለሁ /2/

3. የጨለመን ተስፋ ብሩህ ስታደርገው
የተሰበረን ልብ የሱስ ስትጠግነው
ነፍሴ ይህን አይታ ያላንተ ብላለች
ለህይወቷ እረኛ አንተን አድርጋለች

ካንተ ተለይቼ ወዴት እሄዳለሁ
አንተ የሕይወት ቃል እንዳለህ አውቃለሁ /2/

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top