ጌታ ውለታህ በዛ አንተ ቸር ነህ
ድንቅ ነው ፍቅርህ ወደር የሌለህ
ቅዱስ ነህ እንበልህ /2/
ጌታ ስትጠራ ብዙ ዘርፍ አለህ
አይ ደግነትህ አቅራቢነትህ
ሁሉን ባቅሙ ታሳትፋለህ
እንዲባረክበት መክሊትህን ሰጥተህ
ጌታ ለወዳጅነት ስትጠራ
መጥተን እንድናይ ያለህን ስፍራ
ብልሆች ሆነን ጥሪህን ሰምተን
ስንውል ካንተ ጋር እናውቅሃለን
ጌታ ህይወትህን ሰጥተህ ስትጠራ
በሐሴት የተሞላ ሳይሆን መራራ
በሙላት ኑሩት ብለህ ስትመክረን
ይኸው ላንተ ክብር እንሰዋለን
ጌታ ለቅድስና ስትጠራ
ለዓለም ብርሃን ሆነን እንድናበራ
ቅዱሳን ተብለን ባንተ ተመርጠን
አንተን ትተን ወዴት እንሄዳለን
