መንቃት ይሁንልን

170

ለምንድን መኝታው ማሰሮው ሆኖ ባዶ
መንቃት ይሁንልን አሜን
ዘይትን ፍለጋ ሊሮጥ ጊዜው ረፍዶ
መንቃት ይሁንልን አሜን
ያ ድካምን እንጂ አያስገኝም ሌላ
መንቃት ይሁንልን አሜን
ሙሽራው መጥቶ እንዳይቆጨን ኋላ
መንቃት ይሁንልን አሜን

ቀን ሳለ ንቁ ቀን ሳለ ሩጡ በርቱ
አቅም ይደክማል ያንን አስታውሱ አስታውሱ

ጌታ አሀሀ ኧረ ስንቱን ይታዘበዋል
ጌታ አሀሀ መቼም ስንቱን ይታዘበዋል

ለቤቴ ያለን ቅናት እዩ እንጂ ቀዝቅዞ
መንቃት ይሁንልን አሜን

አይናችን በዓለም ውድድር ላይ ፈዞ
መንቃት ይሁንልን አሜን
አንዴ ስንጠብቀው ገብቶን ህልውናው
መንቃት ይሁንልን አሜን
ቁልቁለት ሲወስደን ደግሞ ፍልስፍናው
መንቃት ይሁንልን አሜን

እግዚአብሔር መጥቶ ባርያውን ፍለጋ
መንቃት ይሁንልን አሜን
በእርሱ ደስ እንዳለው አግኝቶት ሲተጋ
መንቃት ይሁንልን አሜን
መንቃት ይሁን ለኛስ ከመጠፋፋቱ
መንቃት ይሁንልን አሜን
ከዘር ጎሰኝነት ያንቃን በምህረቱ
መንቃት ይሁንልን አሜን

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top