ዕጣህ

172

ከእንግዲህ ላምን ላይገዛኝ ሌላ ሌላ
የሱሴ እኮ ነው ምርጫዬ ለፍጻሜዬ
መንፈሴ በርታ ስጋዬ ቢሆን ደካማ
ሰላም የለህም አምላክህን ከተውከውማ

ዕጣህ(2) ከእግሩ ስር ይሆን መገኛ /2/
ሌላው(2) ለነፍስህ አይሆነህ ዋስትና

ግብህ ምንድነው ስትኖር በዚህ ምድር ላይ
አለምን አትርፎ ነፍስህን ማጣት ነው ወይ ራይ
ይሄ ከንቱ ነው ተው አንተ እንዲህ አትሁን ከቶ
ዕጣህ አድርገው በእግዚአብሔር ቤት መጣልን መቶ

ድርሻዬን አትበል እግርህም ከቤት አይውጣ
በእግዚአብሔር መኖር ይሻላል ሁሌም ያንተ ዕጣ
ወስን መንፈሴ ይበጃል እመን ተረዳ
ልጅነት የለም ሁልጊዜ ለቃሉ እንግዳ

አጥተኸው አትኑር ሞገሱን የክብር ትርፉ
ዛሬም ጊዜ አለህ ተመለስ ግባ ከእቅፉ
ወደርሱ የመጣ ወደውጪ አይጥልም ከቶ
ለነፍስህ ታረም መንፈሴ ይግባህ አጥርቶ

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top