ከልብ አገልግለው

171

መስዋትህን በቅን ልብህ ሰዋ
እንደአቤል ንጹህን አቅርበው
ሽንገላህን እርሱ ይፀየፋል
እግዚአብሔር ኧረ እንዴት ይዋሻል
ከልብ አገልግለው /2/
ጌታን ደስ ይበለው /2/

እምነት የሌለው ባዶ ፀሎት
የከንፈር ብቻ አገልግሎት
እግዚአብሔርስ መቼ ይሻል /2/
ልብህ ለምን ከእርሱ ይሸሻል

ዝማሬህ ልክ ነው ለፈጣሪህ ስራ
ከልብህ ከወጣ ነፍስንም ከዘራ
ግን እርሱ ይንቅሃል ሽንገላህን ተወው
በእውነት በመንፈስ ሆነህ

በፊቱ ሁሉ የበራ ነው
እግዚአብሔር እኮ አዋቂ ነው
ከቶ ማን ከእርሱ ይሰወራል /2/
ሁሉን ያያል ይመዝናል

ማልዶ መውጣቱ ለአምልኮ

ልብን ካልሰጡ ተንበርክኮ
ድካም ነው ትርፉ ፍሬ አይታይ /2/
ቢዘምሩ ከአንገት በላይ

ነቢያት ታምነው አይተውታል
ቅዱሳን ክብሩን ያከብሩታል
ግርማው ሰማይን እንደሞላው /2/
አሜን ይሁን የተገባው

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top