የተሰጠህ መክሊትህን

173

የተሰጠህን መክሊትህን አትርፈሃል ወይስ ቀብረሃል

የተሰጠሽ መክሊትሽን አትርፈሻል ወይስ ቀብረሻል
ከቀበረክበት አውጣና ቶሎ አትርፍ እንደገና
ከቀበርሽበት አውጭና ቶሎ አትርፊ እንደገና

የተከፈለውን በጐልጐታ ይረሳሐል ወይ ያ ውለታ
ተገላቶ ተስቃይቶ የሞተልን በኛ ፈንታ
እዳ አለብህ የጌታችን እንድታተርፍ መክሊትህን
እዳ አለብሽ የጌታችን እንድታተርፊ መክሊትሽን

እንድናተርፍ ተሰጥቶናል እንዳንዘገይ ጊዜው ያልፋል
የጉብዝናው ወር ያበቃል በመሐሉ ጥሪ ይደርሳል
ና እናተርፍ አንተ ወጣት ነገ ስትል ጊዜው ያልፋል
ነይ እናትርፍ አንቺ ወጣት ነገ ስትይ ጊዜው ያልፋል

በመክሊቱ የነገደ ብዙ እጥፍ ያተረፈ
እንድትሆን ባላደራ በሁሉም መስክ ቃሉን ዝራ
ትርፍ ካገኘህ በመክሊቱ ይሰጥሐል ሽልማቱ
ትርፍ ካገኘሽ በመክሊቱ ይሰጥሻል ሽልማቱ

እስከ ዛሬ ተኝቻለሁ የጋን ውስጥ መብራት ሆኛለሁ
አሁን በቃ ነቅቻለሁ ከእግዲህ አበራለሁ
ብለህ ተነስ ቃል ግባና በአጭሩ ታጠቅና
ብለሽ ተነሺ ቃል ግቢና በአጭሩ ታጠቂና

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top