ክብር ለአንቺ ለሰማይ እመቤት
ላኪ ሰላም ፍቅርና ስብሐት
የአዳም ተስፋ የሁላችን እናት
ልባችንን ሰጠንሽ ንግስት
ወጣች ድንገል ተነሳች በአማን
ተቀመጠች በልጅዋ የማን
ዘውድ ደፋች አገኘች መንግስትን
ተዘጋጅቶ የጠበቃትን
ጌታም ደግሞ ሲሰጣት አክሊልን
ደስታዋ እንደምን ይሆን
መከራዋን በምድር ያገኛትን
ለወጠላት ልጅዋ በብርሃን
ቅዱሳንም ተቃጥለው በፍቅርሽ
ዋጋቸው ነሽ አንቺን ሲያገኙሽ
በደስታ ዙሪያሽን ከበቡሽ
አንዲት ደቂቅ ምነው ባየሁሽ
እንግዲህስ እኔንም ጨምሪኝ
እንድሸለም አንቺን እንዳገኝ
ድንቁርና ድካም የከበበኝ
እንድወድሽ ብርሀን አሰጭኝ
ጽጌረዳ የገነት ነሽ መአዛ
አዛኝ አናት የምርኮዎች ቤዛ
ላገራችን ፍቅሯ ላንቺ እንዲበዛ
ብርሃን ስጫት ለጴጥሮስ ትገዛ
ብሩክት ዘር የሃና የኢያቄም
አለሽበት ለአንቺ የሁን ሰላም
ይውረድ ለኛም የፍቅር ዝናም
እንድበቅል እንድንለመልም
