ምስጋና ለማርያም ዘወትር ይገባል
በውነት ከለመንን ደስታ ይገኛል
በአማላጅነቷ በፍቅሯ ደግፋ
ትጠብቀናለች ዘወትር እንዳንጠፋ
ከምድር ፍጥረታት ለዘላለም
እንዳንቺ ያለ ከቶ አናገኝም
ከሴቶች መሃከል የተባረክሽ
ልዑሉን አኖረ በማህፀንሽ
በፍፁም ንፅህና ተሞልተሻል
ለአለም መድሐኒት ተሰጥተሻል
ከአንቺ ትህትናን እንድማር
ማወቅ እንሻለን የአንቺን ክብር
የብርሃን እናት ነሽ የኢየሱስ
በሃይሉ የፀለለሽ መንፈስ ቅዱስ
ለአንቺ ምስጋና ሁሉ ያቀርባል
ከነፍሳት አንስቶ ማን ይቀራል
