ማርያም ጠበቃችን

180

አንቺ ቅድስ ድንግል እግዚአብሔር
የመረጠሽ
ከሴቶች ለይቶ እጅግ አከበረሽ
እኛም እንመካ በእናትነትሽ
መጠጊያ ሆነሻል ለምንለምንሽ

ክብርን ድልን ያገኘሽ
መላክት ያከበሩሽ
ፊትሽ ወድቀን ለመንሽ
ማሪያም ጠበቃችን ነሽ

በዘመነ ኦሪት ሰዎችሐጥያት ሰሩ
የፈጣሪያቸውን ትእዛዝ ያላከበሩ
ስለዚህ መረጠሽ ድልድይ እንድትሆን
አምላክና ሰውን እንድታገናኚ

ችግር ሲደርስብን በጣም ስንረበሽ
ከእግዚአብሔር እንዳንርቅ ትደግፊናለሽ
ፍቅርና ጥበቃሽ ሁሌ አይለየን
ሕይወት ሰላምና ጤና እንዲሆንልን

በልባችን ክፋት ሐጥያት ስንሰራ
በአንቺ አማላጅነት አምላክ ለኛ እራራ
እግዜር በዘረጋው በያቆብ መሰላል
አዳነን ልጆቹን እልል እልል እንበል

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top