ሃሌ ሉያ /5/
አንቺን ሁሌ የለመኑ የተማፀኑሽ
በፈተና ጊዜ ሁሉንም ሰምተሽ
ማንንም ሳትመርጪ ለሁሉም ፈፃሚ
በምድር በሙሉ ሆነሻል ተሿሚ
ለአምላክ አናት ማሪያም ምስጋና እናድርስ
ሁሉም በማመስገን እረድየቷን ይቅመስ
የአለም ፍጥረታት እያሞገሱሽ
ዘወትር በምድር ላይ ይጠራ ስምሽ
ሰላምን ለሚሹ ሰላም ስትሰጫቸው
ክብር ይሰጡሻል የምትደርሺላቸው
ንገሽ እናታችን እንዘምር በእልልታ
ይድረስ ምስጋናችን በአለሽበት ቦታ
ማሪያም እናታችን ውዷ አዛኝቷ
ስምሽን በማሞገስ እንዘምር በእልልታ
ባንቺ አማካኝነት አዳኝ መጥቷልና
ይገባሻል ዘውትር ክብርና ምስጋና
