እኛ ስደተኞች መንገዱ ጠፍቶብን
ጌታ በአንቺ መጥቶ ከጥፋት አዳነን
ግራ ለተጋባው መጠለያ የሆንሽ
የአምላክ ማደሪያ እናታችን ነሽ /2/
የምህረት እናት ሆይ የኛ ጠባቂያችን
ባንቺ ለኛ መጣ አዳኙ ጌታችን
እኛ የሄዋን ልጆች ስደተኞች ሆነን
ጩኸታችንን ስሚን ስንለምንሽ አንቺን
በዚህ በችግር ጊዜ እየተጨነቅን
እያዘንን አንቺን እንማፀናለን
እንግዲህ እባክሽን የኛ ጠበቃ ሆይ
በምህረት ዓይኖችሽ እኛን ተመልከቺ
የዓለም ሁሉ ንግስት አማላጂ ድንግል
የተባረከው የሆድሽ ልዑል
ኢየሱስ ከዚህ ስደት ነፃ እንዲያወጣን
ቅድስት የአምላክ እናት አንቺን ተማፀንን
