መሃሪ አምላክ

241

መሃሪ አምላክ ነህ የኔ ጌታ
ማረኝ እልሃለሁ ጠዋት ማታ
ሰምተህ ዝም አትለኝ ትምረኛለህ
ከክፋት ሃሳቤ ታነፃኛለህ

አንደበቴን ከኃጥያት እንድጠብቃት
በፅድቅና ሰላም እንዳኖራት

ልቤን አበርታና እጄን ያዘኝ
ወደፅድቅ ምድር ጌታ ምራኝ

ከአንተ ሌላ ለኔ ማን አለኝ
ለኔ መልካም ወዳጅ ሚቀርበኝ
ክፉዬን ትቶ የሚምረኝ
ከወደኩበት የሚያነሳኝ

ወደመቅደስህ እስክገባ እኔ
የማላውቅ ደካማ ነበርኩ ያኔ
ግን ባየሁህ ጊዜ ግርምት ሆነኝ
ለኔ ማሰብህን ተረዳሁኝ

እጆቼ በኃጢያት እንዳያድፉ
ሰውን በማታለል እንዳልሆን ክፉ
ከአንተ አይደበቅም ሙሉ ስራዬ
ይቅር በለኝና አንፃኝ ጌታዬ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top