የእግዚያብሔር ቅዱስ ቤተሰብ

184

ኢየሱስ ማርያም ዮሴፍ
የእግዚአብሔር ቅዱስ ቤተሰብ
አብነት ሆነዋል ለዓለም ሁሉ ቤተሰብ

በናዝሬት በእስራኤል አገር ይኖሩ ነበር
በደስታ በስምምነት ቤታቸው ሞልቶ ነበር
ሶስቱ ሲሰሩ ሲፀልዩ በአንድነት ሲረዳዱ
ድንቅ የሆነ የእ/ር ቅዱስ ቤተሰብ ነበሩ

ቤተሰባችን እነርሱን መምሰል የሚገባቸው
ወላጆች ከልጆች ጋር መፋቀር አለባቸው
ሳይቀያየሙ መረዳዳት አለባቸው
በህብረት በሰላም ሆነው መኖር አለባቸው

አለእግ/ር እርዳታ ይህ አይቻልምና
መጸለይ ብዙ ጊዜ መቁረብ ያስፈልጋልና
እርዳታው ሳይጓደልባቸው በሙሉ ሲቀበሉ
በትዕግስት በስምምነት በፍቅር ይኖራሉ

ኢየስስ ማርያም ዮሴፍ ልቤን ነፍሴን እሰጣቹዋለው
ኢየሰስ ማርያም ዮሴፍ በጣር ሞቴ ግዜ እርዱኝ
ኢየስስ ማርያም ዮሴፍ ከእናተ ጋር ልሙት
አሜን……….አሜን…………አሜን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top