እነሆ ትውልድ ሁሉ

185

እነሆ ትውልድ ሁሉ ብፅእት ይሏታል
ብርቱ የሆነው እርሱ በእርሷ ታላቅ ስራ አድርጓል

1. እምነት ፍቅር ተስፋ ጠፍቶ በዚህች አለም
ሰይጣን በፍጥሩ ሲጫወት ዘላለም
ንጽህናን ይዛ በምድር የኖረች
እመቤቴ ማርያም በናዝሬት ተገኘች

እነሆ ትውልድ ሁሉ ብፅእት ይሏታል
ብርቱ የሆነው እርሱ በእርሷ ታላቅ ስራ አድርጓል

2. ተላከ ገብርኤል በቅድት ከተማ
የምስራቹን ቃል በናዝሬት ሊያሰማ
ፀጋ የሞላሽ አላት በታላቅ ትህትና
የማህፀኗ ፍሬ እየሱስ ነውና

እነሆ ትውልድ ሁሉ ብፅእት ይሏታል
ብርቱ የሆነው እርሱ በእርሷ ታላቅ ስራ አድርጓል

3. በገብሬል ንግግር የደነገጠችው
ይሄኛው ሰላምታ ከየት ነው አለችው
ጌታ ከአንቺ ጋር ነው የሰማይዋ እናት
ከሴቶቹ ሁሉ ተመርጠሻል አላት

እነሆ ትውልድ ሁሉ ብፅእት ይሏታል
ብርቱ የሆነው እርሱ በእርሷ ታላቅ ስራ አድርጓል

4. እግ/ር መረጠሽ ለእርሱ ምን ይሳናል
ከድንግል ወንድ ልጅ አዳኝም ይሆናል
ቃና ዘገሊላ ታየ ግሩም ተዓምር
በእናታችን ምልጃ እግ/ር ሲከብር

እነሆ ትውልድ ሁሉ ብፅእት ይሏታል
ብርቱ የሆነው እርሱ በእርሷ ታላቅ ስራ አድርጓል

5. የተመረጥሽ እመቤት እናቴ ነሽ ያላት
የዮሐንስ መልእክት ትዕዛዙ ይህቺ ናት
በርሷ ዘንድ እንድንሄድ እንድንለምናት
የፍጥረት አማላጅ ድንግል ማርያም ናት

እነሆ ትውልድ ሁሉ ብፅእት ይሏታል
ብርቱ የሆነው እርሱ በእርሷ ታላቅ ስራ አድርጓል

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top