ገሯ ማርያም ቸሯእናት
በየሱስ ዘንድ በጌታችን
ገሯ ማርያም ቸሯእናት
ታማኝ ባልደረባችን /2/
ማርያም ተያዥ ዋሳችን
መጠጊያ ምሽጋችን
ድልድይ መሻገሪያችን
ብርቱ አማላጃችን
በዛሬ ቀን ውድ እመቤት
ረድኤትሽን ለማግኘት
ወዳንቺ መጣን የኛ እናት
የምድር የሰማይ ንግስት
አምላክ ከሁሉ አፍቅሮሽ
መቅደሱ አደረገሽ
ኢየሱስ ክርስቶስ ውዱ ልጅሽ
ሆነ ግርማዊው ልጅሽ
ከልዑልም እግዚያብሔር
ባንቺ የሚደርሰን ምክር
እንዲያበቃን ለሰማይ ክብር
ኦ ማርያም ሁኚ መምህር
ከሐጥያትም ስንርቅ
አውጭን ቶሎ አርነት
ቀኑ አይሁንብን ለሊት
ማርያም ሆይ የኛ ህይወት
