ስለኛ ለምኚ

188

1. ወደ ተራራማው ወደ ይሁዳ አገር
ጌታ ያረገውን ወጣች ለመናገር
በአምላክ መመረጥ ከብር ሆኖ ሳለ
ማርያም ለመታበይ ልበሽ መች ከጀለ

ይህን ትህትና ፍቅርሽን በማሰብ
አማልጅን እንላለን በመፀለይ ከልብ
የአምላካችን እናት ፀጋ የምታስገኚ
አሁንም ዘወትር ስለኛ ለመኚ /2/

2. ኤልሳቤጥ ደስ ብሏት በሰላምታሽ ቃላት
መክበሯን ገለፀች በአንቺ ጉብኝት
ለኛም ክብር ይሁን ከቤታችን ገብተሽ
ሰላምታሽን ስጭን በተዋበው ድምፅሽ

እርሱ የሚላችሁን ትዛዙን ፈፅሙ
ብለሽ ተናገሪ ቃሉን ለማይሰሙ
የአምላካችን እናት ፀጋ የምታስገኚ
አሁንም ዘወትር ስለኛ ለመኚ /2/

3. እናቱ እንድትሆኚ ለዚያ ደቀመዝሙር
እየሱስ ሲሰጥሽ በደስታ በክብር
እጅግ ተደሰተ አንቺን በማግኘቱ
ትልቅ ሐብት ሆንሽለት ብርሐን ሞላ ቤቱ

ይኽውልሽ ልጅሽ ብሎ እንዳስረከበሽ
ለኛም እናት ሁኚ ለምንለምንሽ
የአምላካችን እናት ፀጋ የምታስገኚ
አሁንም ዘወትር ስለኛ ለመኚ /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top