የሰማይ ንግስት ዓይኖችሽ
ይረፋበት በዚህ ቤት
ሃጥአንን ማማለድ
መብትሽም ነው በውነት /2/
ከሰይጣን ወጥመድ
አንቺ የአምላክ ባለሟል
ከጥቃቱ ከጥፋቱ
አደራ አደራ ሰውሪን /2/
መሪ ኮከብ ሚዛናችን
ወደ ኢየሱስ አድርሽን
በሰማይ በግርማው
አይተነው ደስይበለን /2/
የኛን ምኞት ፈጽሚልን
ቀኑን ለኛ በመስጠት
ሁልጊዜም የአንቺ ውለታ
ነው የማይዘነጋ /2/
አትበይ ዝም ሲመጣ ሞት
ሳለን እኛ በሐጥያት በመጨነቅ
ከዲያቢሎስ እስር ቤት /2/
አሰጪን ለሁላችን
መንግስተ ሰማያትን
ብሩክት ሆይ ተገን ሁኚን
ዘወትር ዘወትር ዘወትር /2/
