እጅግ ውድ እመቤት አንድ ለት
ልቀመጥ አንቺ ቤት እገነት
ወደሽኛል አንቺ ውድ እመቤት
ያንቺ ፍቅር ልቤን አናወጣት
ያንቺ ሐሳብ ህይወቴን አደሳት
በምድርም ላይ ደስ ያሰኛል በውነት
መች አያለው እመቤት ፊትሽን
ናፍቄያለው እኔም ያንን ቀን
እዳይርቅም ከልቤ ሐዘን
እወዳለሁ ለማዜም ስምሽን
መንገደኛ ሲያስብ ሐገሩን
ይበረታል ሰርክለት በጣሙን
ያንቺ ፍቅር ይልቅ ወጋው ልቤን
ደግሞም አንቺም የኛን ተቀበይን
በመከራ ነፍሴ ስትጨነቅ
ውድ ስምሽ መከራዋን ያርቅ
ስንለምን ያንቺን ክብር ስም
ይሰጠናል ቡራኬ ሰማይም
ለሚጠራው ስምሽ ይጣፍጣል
እኔም ደግሞ ጠራሁሽ ሰርክለት
አውቃለሁ አንቺ ክብርት ድንግል
በፍቅርም አይተሽኛል በውነት
