ኪዳነ ምህረት

198

ቅድስት ድንግል ማርያም
ወላዲት አምላክ
ከአለም ሁሉ ሴቶች መረጠሽ ጌታ አምላክ
በሰማይ በምድር ይወሳል ስላንቺ
የእ/ርን ትዛዝ አከበርሽው አንቺ

ኪዳነ ምህረት ባላደራችን ነሽ

የታመነ ዋስትና ከኢየሱስ ተቀበልሽ
ተስፋ ነሽ ለሰው ልጅ ያኔ ሆነ ድሮ
ከገነት ሲወጣ አዳም በትልቀ እሮሮ

የአምላካችን እናት ቅድስት ነሽ እኮ
ልቤ ተማረከ በፀጋሽ ተልኮ
ለዘለአለም ልኑር ከአንቺ ጋር በሰማይ
ልጃን ለሰዋልኝ እግዚያብሔርን ላይ

አንፀባራቂ ፊትሽ ከፀሐይ የላቀ
የውበትሽ ለዛ አማረ ደመቀ
ኪዳነ ምህረት አንቺ ነሽ ከላይ
ታማልጅናላሽ በላይ በሰማይ

ጭንቅት ቢሰማሽ ልጅሽ ሲሰቃይ
ፅናቱን ላከልሽ ጌታ ከሰማይ
ጭንቀትሽ ቀጨጨ በትእግስት ተውጦ
በእምነትሽ ብዛት በደስታ ተበልጦ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top