የፍቅር ንግስት ሆይ ለኛ ለምኝልን
ማርያም እመቤት ሆይ ሰላምን አሰጭን
በአለማች ላይ ሰላም እጅግ ጠፍቷል
ፍቅርና ደስታ እጅግ እርቀውናል
ረሐብና ጥማት ተደራርቦብናል
ማርያም ሆይ እርዳታሽ በፍጥነት ያሻናል
ምቀኝነት ጠፍቶ መዋደድ እንዲስፍን
ትእቢት ተወግዶ ትህትና እንዲነግስ
ጦረነት ተረስቶ ሰላም እንዲታወስ
ማርያም ሆይ ወዳንቺ ፀሎታችን ይድረስ
የሰላም ንግስት ሆይ አስታወሽን እባክሽ
በዚህ በስደት ላይ ያለነው ልጆሽ
እረፍትም አጥተን የምንማፀነሽ
ፀሎታችን ይድረስ ይሰማ ለልጅሽ
ሰላሜን እሰጣለሁ ብሏልና ልጅሽ
ያውርድልን አሁን ሰላሙን እባክሽ
እርሱ እንደወደደን እንድንዋደድ
አንቺ በመራሽን እንድንራመድ
