እኛ የምናከብራት

199

እግዚአብሔር እንዲህ አለ ሰይጣንን ሲረግመው
ባንተና በሴቷ ጠብን አደርጋለሁ
ከሷ የሚወለደው የመጥፊያህ ምክንያት ነው
ራስህን ሊቀጠቅጥ ሥልጣን እሰጠዋለሁ
ሴትን እንዳሳትክ ከሴት እመጣለሁ

የጌታ ቃል ይላል ትውልድ ሁሉ ያከብራታል
ታዛዥ ስለሆነች ፈርሃ አምላክ ያላት

የመልአኩን ቃል ሰምታ የተቀበለች
ያለመጠራጠር ፍቃድህ ይሁን አለች

የኢየሱስ እናት እኛ ምናከብራት
እግዚአብሔር አባት መርጦ ስላገኛት
የልጁ ማደሪያ ታቦት ስላደረጋት
ፀጋን የተሞላሽ ንፅሕት በለአላት

አንዳንዶች ቢሏትም በአፈ ታሪክ ያለች
መዳን እንድናገኝ ምንም ያላረገች
እኛ ግን ብለናል እግዚያብሔር ሲመርጣት
በደህንነት ሚስጥር ታላቅ ስፍራ ሰጣት

ከሷ ስጋ ሆኖ ያ ቃል አከበራት
ይችህን እናት ነው እኛ የምናከብራት
አፈ ታሪክ ሳይሆን የጌታ ምርጫ ናት
የቃሉ ማደሪያ እንድትሆን ሲመርጣት
ከሴቶች መካከል የተባረክሽ አላት

ስጋውና ደሙን ኢየሱስ የሰጠው
ከማርያም ያገኘው ያካሏ ክፋይ ነው
ዘጠኝ ወር በሆዷ ይዛው የኖረችውን
ደምና ስጋዋን ሰጥታ የወለደችውን
እንዴት አናክብራት እንዲህ የታደለችውን

ጨረቃን በእግሯ ስር አድርጋ ያጌጠች
አስራሁለት ክዋክብት በራሷ የደፋች
ልጇ የሚገዛ የሰማይ ሰማያት
ልኡል እግዚአብሔር ሥፍራ ያዘጋጀላት
እንግዲህ እወቋት ማርያም ናት የኛ እናት

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top