እመቤቴ ሆይ /4/ በሁሉ ነገር አግዘሽናል
ከክፋ ነገር ጠብቀሽናል
ስለዚህ ለአንቺ ክብር ይገባሻል /4/
ማርያም ስምሽን አመስግነን ስንጠራ
ይሄው አልፈናል ብዙ መከራ
ድንግል እንዝምር ላንች እንደገና
እኛም ጠብቂን ከአለም ፈተና /2/
በመከራችን ደግፈሽናል
ተክዘንም ሳለ አፅናንተሽናል
የክብር ንግስት እናከብርሻለን
ለስምሽ ሁሌ እንዘምራለን /2/
ስምሽን ስንጠራ እኛ አማረብን
ከዚህም በላይ ፀጋን አብዥልን
እምዬ በአንቺ ሁሉንም አልፈናል
በአንቺ ተማምነን እዚህ ደርሰናል /2/
እዚህ ደርሰናል
