የጌታችን እናት ለመሆን የበቃች
የዘለአለሙን አምላክ ለእኛ ያደለች
ልጇን ለሰው ልጆች ማዳን የሰጠች
ከጌታ ጋር በእውነት ታስታርቀናለች
የሰላሙ እናት ንጉስ የሆነች
ለአለም ሁሉ ብርሃን ያደለች
የመላእኩን ቃል ባትቀበል ኖሮ
ሁላችን ጠፊ ነን ከዚህ አለም ንሮ
የመዳን ጐዳና በእርሷ ተጀመረ
የአለም ህዝብ ሁሉ በልጇ ከበረ
ባለንበት ምድር ተረስትን ነበረ
በማርያም ያደረ ጌታ ታሪክ ቀየረ
አለችን እናት ያለሐጥያት የተፀነሰች
ምንግዜም ዘወትር ድንግል የሆነች
የተገባ ምላሽ መስጠት እንደሚገባን
እንዳልከው ይሁን ብላ ያስተማረችን
የማይጠገብ ፍቅር የለገሰችን
እሺታ ለልጆቿ ያስተማረችን
