አዲሲቷ ሔዋን እናታችን/2/
ተካፋይ የደህንነታችን /2/
ባለሙሉ ፀጋ ባለሙሉ ሰላም
ከአምላክ የተሰጠች እርሷ ናት ማርያም
ማርያም የአምላክ እናት /4/
ፅዮን ታዛዥ እመቤት /4/
ያዕቆብ በካራን ድንጋይ ተንተርሶ
አለመ መሰላል ወደ ሰማይ ደርሶ
የበረከት ምንጭ በምድር ተገኘች
ሰውን ከአምላክ ጋር አስታረቀች
አለብን ውለታ ከበሮ ይመታ /2/
አለብን ውለታ ይጨመር እልልታ/2/
በኮሬብ ተራራ ሙሴ እንደታየው
በእሳት እያለፈ እንዳልተቃጠለው
የሙሴ ቁጥቋጦ የመንፈስ የፅላት
ለአዳም ቃል ኪዳን የእግ/ር መልስ ናት
