አንድ ነገር አንድ ነገር አለሽ
ከሴቶቹ ለየት የሚያደርግሽ
እግዚአብሔር በሞገሱ ያየሽ
በክብር ላይ ክብር ያለበሰሽ
ማርያም የተባረክሽ ነሽ /2/
ማርያም የተለየሽ ነሽ
ለእርሱ የተለየሽ ነሽ
1. በመልኩ ምሳሌ በአምሳሉ ከሰራው
እግ/ር ፍጥረቱን በምድር ሲሞላው
ሰማያዊ ንግስት አንቺን ካረገሽ
አንድ ነገር አለ እንዲህ ያስወደደሽ በልብሽ
አንድ ነገር አንድ ነገር አለሽ
ከሴቶቹ ለየት የሚያደርግሽ
እግዚአብሔር በሞገሱ ያየሽ
በክብር ላይ ክብር ያለበሰሽ
ማርያም የተባረክሽ ነሽ /2/
ማርያም የተለየሽ ነሽ
ለእርሱ የተለየሽ ነሽ
2. ስንቱን ባስደመመ ስንቱን ባስተማረ
በታላቅ መታዘዝ ቃልሽ ለእርሱ አደረ
ከሴቶች ለይቶ እንዲህ ያደለሽ
አሜን ለዘለአለም በስራው ትክክል ጌታሽ /
አሜን ለዘለአለም እንከን አይወጣለት ጌታሽ /2/
አንድ ነገር አንድ ነገር አለሽ
ከሴቶቹ ለየት የሚያደርግሽ
እግዚአብሔር በሞገሱ ያየሽ
በክብር ላይ ክብር ያለበሰሽ
ማርያም የተባረክሽ ነሽ /2/
ማርያም የተለየሽ ነሽ
ለእርሱ የተለየሽ ነሽ
