ማርያም እናቴ የብዙዎች መጠጊያ
አምናለሁ ልዩ ነሽ የመለኮት ማደሪያ /2/
ተስፋቸው አንቺ ነሽ ለቀረቡሽ
አማልጅን እያሉ ለሚማጸኑሽ
በእናትነትሽ እተማመናለሁ
እኔም ተንበርክኬ አማልጅኝ እላለሁ
እማፀንሻለሁ
በአርያም ያለው ገናናው ልጅሽ
ጥያቄ ሲኖርሽ መልስ የሚሰጥሽ
ቃና ዘገሊላ መቼ አሳፈረሽ
ጊዜው ባይደርስ ደስ ያሰኘሽ
የታዘዘልሽ
ስምሽ ስንቅ ይሆናል ወዳጅ እናታችን
ክብርሽ ከፍ ይበል በዓለማችን
ያሬድ በመዝሙሩ ከአፉ ያለየሽ
ዛሬም ለዘላለም እኩያ የሌለሽ
አቻ አይገኝልሽ
ኢየሱስን ይዘሽ ወደ ኤለሳቤጥ
ዕርዳታ እንደምትሻ ለማረጋገጥ
በመንፈስ ተረድቶ ጽንሱ ሲሰግድልሽ
ትንቢት ተናግረሻል ለመመረጥሽ
ድንግል እናት ነሽ
