አዲስ ጥላ መጠለያ
ለእግዚአብሔር ልጅ ቤት ማደሪያ
ማርያም ሆነች ብቁ እናት
ፍፁም እንከን የሌላት /2/
የዋህነት የሞላት
ታዛዥነት የሞላት
- የእግዚአብሔር ልብ ዕረፍት ንፁህ ሴት
አንድ ሆና የተገኘች ከፍጥረት
ቅድስት ንፅህት ማርያም ናት
ጌታ ለሱ ሥራ የሠራት /2/ - ባዳም ሥራ የጠፋው ዘር ሲፈላ
ሊበራ ሊገፈፍ ያ የሞት ጥላ
ባምላክ ፀደቀች ማርያም ለእናት
ለማዳን ሥራ ማረፊያ ቤት /2/ - የዘመናት ለቅሶ መማረር
ሰው ጭንቁ ሊያበቃ በእግዚአብሔር
ከሱ ለእሱ ሆነች ማርያም ታይታ
የሱስን የያዘች ለአደራ በቅታ
