ብዕእት ነሽ

215

ከቶ ከእንስት እንደ ልቡ ያገኘው ማንን ነው
እግዚአብሔር አለምን ሲጎበኘው
በቅን ልብሽ ማሪያም ተደነቀብሽ
ለዘለአለም የተመሰገንሽ ሆነሽ

ብፅእት ነሽ ማሪያም
ንጽህት ነሽ ማሪያም
ከሴቶች ሁሉ ማሪያም
ልቀሽ አለሽ ማሪያም

በቅድስና በእርሱ ጎዳና
ፍጹም የሔደ መገዱ ቀና
የእንስቶች እራስ ኣንቺ ነሽ ማሪያም

የኢየሱስ እናት ምግባረ ሰላም

እግዚአብሔር አለ ጸጋን የሞላሽ
በአንቺ አደረ አንቺን የሰራሽ
እንከን አይወጣ በምርጫው መንገድ
ልብሽን ላየ ለእግዚያብሔር አይከብድ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top