ታዛዥ ቅን አገልጋይ የፍቅር ምሳሌ
እንደአንቺ ማርያም በሆነ እድሌ
ጌታን ማገልገሌ
ልቡ አረፈና ጌታ አንቺን ማግኘቱ
ከሰማይ መጣልን ሊታይ በሱነቱ
እግዚኣብሔርነቱ
በጅማሬው ጌታ ሲጠራሽ
ለእርሱ ሥራ እንደዚህ ወዶሽ
እደረገሸ ለፍጥረት ምሳሌ
ቅን አገልጋይ ለአዳም ዘሮች ፍሬ /2/
ባሳየሽው እምነት በስራሽ
ትዘከረ ለትውልድ ስምሽ
ድንግል ማርያም የአንቺ ስብእና /2/
ያስገርማል ዛሬም እንደገና
በሚቃጠል በከንቱ ፍሪዳ
በባዶ ልብ ለሱ ከሚሰዋ
ከዚህ ሁሉ መታዘዝ ይበልጣል
ይህም እመነት ማርያም ባንቺ
ሆኗል /2/
